The Eagle/By Alfred, Lord Tennyson/translation into Amharic By Alem Hailu/(ንስሩ/በሎርድ ቴኒሶን፡ ትርጉም በዓለም ኃይሉ ገ/ክርስቶስ)
The Eagle
He clasps the crag with crooked hands;
Close to the sun in lonely lands,
Ring'd with the azure world, he stands.
The wrinkled sea beneath him crawls;
He watches from his mountain walls,
And like a thunderbolt he falls.
ንስሩ
የአባጣ ጎርባጣውን ተራራ ጎድን
ወጣ ያለውን አግጥጦ
በተቆለመሙ እጆቹ ቆንጥጦ
በዚያ ለፀሐይ
ጎረቤት በሆነው ወና ሰማይ
ደምቆ
በሰማያዊው ዳራ
ይስተዋላል ገዝፎ በሙሉ ቁመና
ክብ እንደሰራ፡፡
ታች እሱ ካለበት ከተራራው ስር
ቀለበት ቀለበት እየሰራ
የሚተነፍሰውን ባህር
ቓኝቶ በአንክሮ
እንደመብርቅ ክንድ ተገንጥሎ
ይወርዳል ቁልቁል ተወርውሮ!
Philipos
Sat 23rd Nov 2019 12:10
Powerful piece. ?